ተዋሕዶ ቤተ መጻሕፍት (Orthodox Library)

A Digital Resource for Theological Education and Spiritual Growth

በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው ሲሉ የተመድ ዋና ጸሃፊ ገለፁ

 በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ እና ሁከት እና ውድመት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሱ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።

በየቀኑ ንፁሃን ዜጎች እየሞቱ ነው ያሉት ዋና ፀሃፊ፣ “የውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ግጭት ዓለም አቀፋዊ ይዘት እየያዘ በመምጣቱ የፀጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ሁሉም አካላት ሊያስቡበት ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል።